Saturday, 19 July 2014

እንጽፋለን ገና!!!



እንጽፋለን ገና!!!
የክፉ ተኩላን ግፍ የበደሉን ጉዳይ
እንፅፋለን ገና በየመንገዱ ላይ፡፡
ቁራሽ እየበላን ድንጋይ ተንተርሰን
ስጋው የረገፈ ምልምል እንጨት መስለን
እንፅፋለን ገና በእንባችን አጥቅሰን፡፡
ብዕር ቢጠፋብን
ቀለም ቢደርቅብን
ብራና ቢቸግር ቢያልቅ ወረቀታችን
እንጽፋለን ገና በየግንባራችን፡፡
የጋፍነውን ምሬት ያማጥነውን ሲቃ
ወረቀት ቢቸግር ብራና ባይበቃ
የሆነውን መሆን ያየነውን ስቃይ
እንጽፋለን ገና በየመንገዱ ላይ፡፡
የጅቦቹን ዝርፊያ የመድሎውን አቅም
የዘር ማጥራቱንም የኑሮውን ሸክም
በአጥንታችን ብዕር ከትበነው ለአለም
እንጽፋለን ገና በደማችን ቀለም፡፡
ታሪክ እንዳይስተው የኖርነውን ስቃይ
እንጽፋለን ገና መቃብራችን ላይ፡፡

No comments:

Post a Comment