Wednesday, 30 April 2014

የጎሰኞች መሰብሰቢያ ጎጆ የሆነው ኢህአዴግ ይፍረስ!!!




የሚያስቡት በአይምሯቸው ሳይሆን በሆዳቸው ስለሆነ ሰው ሁላ የሚኖረው እንደነሱ በእህል ብቻ ይመስላቸዋል :: ከሥጋዊ ምቾት በባሰ በህሊና ረሃብ የሚሰቃዩ ዜጎችን ጩኸት ለመረዳት አይምሯቸው በስብ ስለደለበና የጆሯቸው ብራና በጮማ ስለተሸፈነ የማዳመጥ ችሎታ ፈፅሞ የላቸውም:: የእነሱ እርካታ ሆድን በመሙላት ብቻ በባዶ ኳኳታ ጭንቅላትጠቅጥቆ፤ በወያኔያዊ ፕሮፓጋንዳ ሕዝብን በማደንዘዝ፤ የአገር ሃብት መዝረፍና ማዘረፍ፤ ሕዝብ በረሃብ እየረገፈ፤ በንቅዘት (ሙስና) ተዘፍቆ የጉራ ልማት ማውራት፤ ደሃ ገበሬዎችን ከመሬታቸው አፈናቅሎ ለቀማኛ የውጪ ከበርቴ መቸብቸብ፤ አዱሱን ትውልድ እዳ ከፋይ በማድረግ ኢትዮጵያን በብድር ማጥ ውስጥ መክተት፤ ዘረኝነት መመሪያቸው፤ ውሸት ክብራቸው፤ ክህደት ኩራታቸው፤ ሽብር ተግባራቸው፤ ጎሰኝነት ባንዲራቸው፤ ሃቅ ተናጋሪዎችን ጠላታቸው፤ ባደረጉባት የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሃቅን መናገር እና መጻፍ አሸባሪ ተብሎ ያስከስሳል::  ጠብ መንጃ በእጁ የያዘ አሸባሪ ባሸበረ፤ ብዕር የጨበጡ ሠላማዊ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች አሸባሪ ተብለው ታሰሩ::
ይህ ኢትዮጵያውያንን በዘር በመከፋፈል ሲያናቁር የኖረው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝበቃህሊባል ይገባዋል፡፡ በመካከላችን ያለውን የጥልና የመከፋፈል ግድግዳ አፍርሰን የሌላው ነጻነት ማጣት የእኛ መሆኑን በመገንዘብ እጅ ለእጅ ተያይዘን ብሔራዊ ዕርቅ በማድረግ በህብረት የምንቆምበት ጊዜ አሁን ነው፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን ጎረቤትና ወዳጅ በመሆን በምንኖርበት መሬት ላይ ኑሮን የምንካፈል ብቻ ሳንሆን ከአያት ቅድመ አያታችን ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣ አንድ ደም የተቀዳን የአንድ ቤተሰብ አባላት ነን፡፡ኢትዮጵያዊነታችንም ለሙሐመድ ለሙሴና ለክርስቶስ የሚጨሰው ዕጣን በእርገት መጥቆ የሚደባለቅበት እምነት ነው፡፡ይህ እምነታችን ከገዢዎች የሚለገስ ወይም የሚከለከል ሳይሆን ፈጣሪ ስንወለድ ጀምሮ የሰጠን የራሳችን የሆነ ማንም ሊደፍረው የማይችል መብታችን ነው፡፡ አገር እየወደመ፣ ሃይማኖት እየረከሰ፣ ዲን በርካሽ እየተሸጠ፣ መስጂድና ገዳማት እየፈረሱ ለመለያየትና የጎሪጥ ለመተያየት ጊዜ ሊኖረን አይገባም፡፡ አዲሲቷን ኢትዮጵያ የምንገነባው በውሸት፣ በጽንፈኝነት፣ በአስመሳይነት፣ በመፈራራት፣ በማጭበርበር፣ አንዱን ከሌላው የበለጠ ወንጀለኛ በማድረግ ሳይሆን ከሁሉ በፊት ሰብዓዊነትን በማስቀደም ብቻ ነው፡፡
ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ!!!!

No comments:

Post a Comment